እንኳን በደህና ወደ ማዳበሪያ ዲጅታል ማሳለጫ ገጽ በደህና መጡ
ይህ የዲጅታል ሥርዓት አገራዊ የማዳበሪያ አቅርቦትን በመሠረታዊነት ለመቀየር በሚደረገው ጉዞ የተደራጀና ወቅታዊ መረጃን የሚያሰባስብ፣ የሚተነትንና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔን መስጠት በሚያስችል መልኩ ተግባር ላይ እንዲውል ታልሞ የተዘጋጀ የመጀመሪያው የዲጅታል ልማት ምዕራፍ ነው፡፡ በሂደቱም በልማቱ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮቻችንንና አልሚዎቻችንን ይበልጥ ተጠቃሚ በማድረግ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ጉልህ አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡
ይህ የግብርና ግብዓቶችን በተለይም የማዳበሪያ አቅርቦትን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት፣ ለመከታተልና ወቅታዊ ውሳኔዎችን ለመስጠት እንዲያስችል ታልሞ የተነደፈ አዲስ የዲጅታል ሥርዓት ነው፡፡ በማዳበሪያ አቅርቦቱ ላይ የሚሳተፉ አካላትን በማስተሳሰር የመረጃ ልውውጣቸው እንዲሳለጥ፣ ግልጽ አሠራር እንዲሰፍን፣ በተደራጀ መረጃ ላይ ተገቢው ውሳኔ እንዲሰጥ፣ የተዝረከረኩ አሠራሮች እንዲቀሩ፣ የአፈር ማዳበሪያ ተጠቃሚው አርሶ አደር በሚያስፈልገው ጊዜ ሁሉ ማዳበሪያ እንዲደርሰው ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥር ዘንድ ለምቶ ወደሙከራ ተግባር የተሸጋገረ ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ነው፡፡
በአፈር ማዳበሪያ አቅርቦቱ ላይ የተሰማሩ ልዩ ልዩ አካላትን ማለትም አርሶ አደሩን፣ የልማት ሠራተኛውን በየእርከኑ ያሉ መስተዳደሮችን (ቀበሌዎች፣ ወረዳዎች፣ የዞን አስተዳደሮችና ክልሎችን)፣ መሠረታዊ ማኅበራትን፣ ዩኒየኖችን፣ የመጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጡ አካላትን፣ መጋዘኖችን፣ በሂደቱ ላይ ቀጥተኛ ውሳኔ በመስጠት ተሳትፎ የሚያደርጉትን አካላት በሙሉ አስተሳስሮ የሚይዝ ሆኖ የተዘጋጀ ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ነው፡፡
ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚፈስበት የአፈር ማዳበሪያ በተገቢው መልኩ ለታለመለት ዓላማ ይደርስ ዘንድ ይህ የዲጅታል ሥርዓት ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት ሆኖ በሂደቱ የሚሳተፉ ሰፊ አካላትን የዲጅታል ክህሎት አቅም በማሳደግ በቀጣይ ለሚኖሩ የዘመናዊ ግብርና ትግበራዎች ፈር የሚቀድ ሆኖ ያገለግላል፡፡
ቅኝት ክልሎች ዞኖች ወረዳዎች ቀበሌዎች መንደሮች ዩኒየኖች ማዳበሪያ ማራገፊያ ጣቢያዎች መሠረታዊ የሕ/ሥራ ማኅበራት የሥርጭት ጣቢያዎች ተሳታፊ ተቋማት የማዳበሪያ አቅርቦት ሰንሰለት የአፈጻጸም ሪፖርቶች ለልጆች
Mengistu Tesfa Lake Lead Executive |
Zewidu Sime Expert |
Belete Berhane Habteyes Expert |
Melese Bedane Begna Desk Head |
Zemenu Menale Expert |
Shimelis Eshetu Expert |
Tiblets Fetsum Girmay Expert |
bizuayhew abebaw Expert |
Oumer Hussen Muhye Expert |
waltengus getachew Expert |
Habib Temam Expert |
Abebe Eshete Expert |
Mengistu Tesfa Lake Lead Executive |